Announcement የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም

የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም

12th July, 2026

### የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ከአሰልጣኞች ጋር ገመገመ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስራና ክህሎት ቢሮ የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ፣ ከጠዋቱ የማኔጅመንት እና የአካዳሚክ ኮሚሽን (ኤሲ) ውይይት በመቀጠል ከሰዓት በኋላ ደግሞ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከኮሌጁ አሰልጣኞች ጋር የጋራ የግምገማ መድረክ አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ላይ ባለፉት 12 ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና የስልጠና አሰጣጥ ሂደቶች፣ የስልጠና ጥራትና አግባብነት፣ እንዲሁም የተመራቂ ሰልጣኞች የሞዴል እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ዝግጅት አፈፃፀሞች በዝርዝር ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። አሰልጣኞች በበኩላቸው በ2018 የስልጠና ዘመን ያጋጠሟቸውን የስራ ላይ ተግዳሮቶች፣ የተመዘገቡ ጠንካራ አፈፃፀሞችን እና በቀጣይ የስልጠና አሰጣጥ ላይ መሻሻል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ገንቢ ሀሳቦችን አንስተዋል።
ይህ ከአሰልጣኞች ጋር የተደረገው ጥልቅ ግምገማ፣ ኮሌጁ ለ2019 ዓ.ም ያዘጋጀውን የ90 ቀናት የንቅናቄ ዕቅድ በተጨባጭ መሬት ላይ ለማውረድ እና የተቋሙን የማሰልጠኛ ወርክሾፖች በስታንዳርድ በማደራጀት ብቁ የሰው ኃይል የማፍራት ተልዕኮውን በስኬት ለመወጣት ጉልህ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።

 

.

Copyright © All rights reserved.

Created with