እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
ትልቅ ስኬት ለደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ!
ኮሌጃችን የትምህርት ጥራትን፣ የተቋማዊ አሰራር ብቃትን እና የሰልጣኞችን እርካታ ለማረጋገጥ ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት የ ISO 21001:2025 (Educational Organizations Management
System) ዓለም አቀፍ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (Certification) ባለቤት መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን!
ይህ
ስኬት የኮሌጃችንን የሥልጠና ጥራትና ደረጃ ወደ ላቀ ዓለም አቀፋዊ ደረጃ ያሸጋገረ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
የምስጋና መልእክት
ይህ
ታሪካዊ ፍጻሜ እውን እንዲሆን ላበረከቱት የማይተካ አስተዋጽኦ ለመላው የኮሌጃችን ማህበረሰብ እና አጋር አካላት ምስጋናችንን እናቀርባለን፡
ለኮሌጃችን አመራሮች፣ አሰልጣኞች እና ሰራተኞች፡ በቅንጅት፣ በቁርጠኝነት እና የጥራት ደረጃዎችን በመጠበቅ ላሳያችሁት ከፍተኛ የሙያ ብቃት እና ድካም ታላቅ ክብር እና ምስጋና ይገባችኋል።
ለአጋር አካላት እና ባለድርሻ አካላት፡ በሂደቱ ሙሉ ጎናችን በመቆም፣ በቴክኒክ እና በሙያዊ ድጋፋችሁ ለሰጣችሁን ያልተቋረጠ እገዛ ምስጋናችን የላቀ ነው።
የጥራት ጉዞ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ፣ ይህንን ዓለም አቀፍ እውቅና አስጠብቀን በመቀጠል የበለጠ ውጤታማ እና ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ለመስጠት ቃል እንገባለን።

.