Announcement ሙስናን እና ሌብነትን መከላከል

ሙስናን እና ሌብነትን መከላከል

23rd August, 2026

ሙስናን እና ሌብነትን ለመከላከል የሚረዱ ቁልፍ መሳሪያዎች
1.  ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር (interanal control) - የገንዘብ፤የንብረትና የስራ ሂደቶችን በደንብ መቆጣጠር ፡፡
2.  የውስጥና የውጭ ኦዲት - የሂሳብና የሀብት አጠቃቀምን በገለልተኛነት መመርመር፡፡
3.  ግልፅነትና ተጠያቂነት -ውሳኔዎች ግዥዎችና የገንዘብ አጠቃቀም ግልፅ እንዲሆኑ ማድረግ ፡፡
4.  የግዥ ሥርዓተ ቁጥጥር - የጨረታ ፤ኮንትራትና የክፍያ ሂደቶችን በጥበቅ መቆጣጠር
5.  የንብረት ቁጥጥር - ንብረትን መመዝገብ መመርመርና በየጊዜው ቆጠራ ማድረግ
6.  የሥራ ክፍፍል(Segregation of Duties) --አንድ ሰው ግዢ ክፍያ ምዝገባና ማጽደቅን ብቻውን እንዳይቆጣጠር ማድረግ
7.  የጥቆማ ሥርዓት (Whistleblowing)  - ሙስናን ወይም ሌብነትን የሚጠቁሙ ሰዎችን የሚጠብቅ የጥቆማ መስመር መዘርጋት
8.  ዲጂታል ሥርዓቶች - የክፍያ ፤የግዥ፤ የንብረትና የሰነድ ሂደቶችን ዲጂታል ማድረግ
9.  የጥቅም ግጭት መቆጣጠር (Connflict of interest  - ሠራተኞች የግል ጥቅማቸውን በስራ ውሳኔ ላይ እንዳያሳድሩ ማድረግ
10.  የስነምግባር ደንብና ስልጠና --- ሠራተኞች የሥነምግባርና የፀረ ሙስና  መርሆዎችን እንዲያውቁ ስልጠና መስጠት
11.  የሥራ ሂደት ክትትልና የአደጋ ግምገማ -- ሙስና ሊፈጥርባቸው የሚችሉ የስራ ክፍተቶችን ቀድሞ መለየት
12.  ጠንካራ የሕግ አፈፃፀም -- ጥፋት ሲገኝ በሕግ መሠረት ፈጣንና ፍትሀዊ  አርምጃ መውሰድ ናቸው ::
            
የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ  የስነ-ምግባርና
 ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት
ነሀሴ 13 ቀን ፣ 2018 ዓ/ም

.

Copyright © All rights reserved.

Created with